ሃይለማርያም ደሳለኝ በመውጫቸው ሰዓት

በቀናት ውስጥ የቀድሞው የሚል ቅጥያ የሚጨመርላቸው ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከዜና መክፈቻነት እየራቁ ተተኪያቸውን ለመምረጥ የሚደረገው ፍትጊያ ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰነባብቷል።

ፓርቲአቸው ባ’ፈቀላጤው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አማካይነት “የግንባሩን አንድነት ያጠናከረ]” ያለው ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ በምስጢራዊነት የታጀለ ስብሰባ እነበረከት ስምዖንን፥ሥዩም መሥፍንን፥አዲሱ ለገሰን፥እንዲሁም ወትሮ የማይታዩት የክፉ ቀን ደራሽ ዶ/ር ካሡ ኢላላንና የመሣሠሉትን ከፊት አሰልፎ ስብሰባውን አጠናቋ’ል።

አዲሱ ሰው ከመሰየማቸው በፊት ግን የሕወሓት ልሳኖች የሃይለማርያም ደሳለኝን ሃጢያቶች በመዘርዘር ላይ ተጠምደዋል። “ደካማ”፥“ልፍስፍስ” ከሚሉ ቅጥያዎች በወንጀል መጠየቅ እንደሚገባቸው እስከመጠቆም የሚደርስ ዘመቻ ከፍተውባቸዋል። አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው።

የጠ/ሚ/ሩን “ሌጋሲ” እንደሚፈትሽ የሚያትተው በሕወሓቶች የተለቀቀ አንድ ፅሁፍ “ፈተና ሲያጋጥማቸው መወሰን የማይችሉ ብቻ ሳይሆን ፈጥነው ውሳኔ መስጠት የማይችሉ ደካማና ልፍስፍስ መሪ የነበሩ መሆናቸው”ን ያትታል። ጠ/ሚ/ሩ በአስቸጋሪ ሁኔታ ሥልጣን የያዙበት ሁኔታና ቀጥሎ የነበሩት አንዳንድ ቴአትሮች ለምሳሌ የወ/ሮ አዜብ መሥፍን ከቤተ መንግሥት አልወጣም ማለትን ያስታወሰ የሚገነዘበው ሙሉ ሥልጣን እንዳልነበራቸው ነው። ለዚህም ይሆናል በራሳቸው ጥረት ከገጠራማው የአገሪቱ ክፍል ተነስተው የዩኒቨርሲቲ መምህርነት ብሎም ዲንነት ደረጃ የደረሱት ምሁር በሕወሓቶች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ዕቅዴ የመለስን ራዕይ ማሳካት ነው ብለው ሲገዘቱ የነበረው።

ጠ/ሚ/ሩ በመጨረሻ ያጡት ሥልጣናቸውን ብቻ ሳይሆን ከአንጋሾቻቸውም ከህዝቡም ሳይሆኑ ገና አራት ኪሎን ሳይለቁ ከፍና ዝቅ መደረጋቸውን ነው። አስተዳደራቸውን “መንግሥት መንግሥት እንዳይሸት ከማድረጋቸውም ባለፈ ህግንና ሥርዓትን ማስከበር የማይችል በራሱ ዜጎች የማይከበር በጠላትም የማይፈራ ልፍስፍስ መንግሥት ሆኖ እንዲታይ አድርገውታል።” ተብሏል በዚሁ መጣጥፍ።

በቅርቡ የተለቀቁትን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት፥ የመብት አራማጆች እንዲሁም ጋዜጠኞችን በሙሉ ሰብስቦ እንደገና ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ሰሞኑን በተለያዩ የሕወሓት ልሳኖች የሚለፈፈውን በሚያጠናክር መልኩ “የፖለቲካ እስረኞችን እንፈታለን በማለት የወሰዱት እርምጃ የሚመሩት(ን) መንግሥት ክብር ዝቅ ያደረገ ታሪካዊ ስህተት ነበር።” ሲል ጠ/ሚ/ሩን ይተቻል። ከዚህ በግልፅ የምንረዳው እስረኞቹን ለመፍታት በሕወሓት በኩል ፈፅሞ ፍላጎት እንዳልነበረ ነው። እንደውም የእስረኞቹ መፈታት ጠ/ሚ/ሩን “በዚህ ደካማ የአመራር ብቃታቸው ምክንያት ስርዓታቸውን ለማፍረስ ሌት ተቀን ሲረባረቡ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ለሚሉ የውጪ ሀይሎች እጃቸውን” መስጠት እንደሆነ በሕወሓት በኩል ያለውን አመለካከት ያሳያል።

ስለአስቸኳይ ጊዜም ሆነ ስለገዢዎቻችን ስብሰባ አቶ ሲራጅም ሆኑ አቶ ሽጉጤ መግለጫ ሲሰጡን ጉዳዩን አውቀውት ሳይሆን ኢህአዲግ ማለት ሕወሓት ብቻ አለመሆኑን ለማስረዳት ጌቶቻቸው የሚጠቀሙበት ሥልት እንደሆነ ግልፅ ነው። ዕውነቱን ለመናገር ግን በመካከለኛ ደረጃ ያለ አንድ የሕወሓት ካድሬ ደአህዲግ ከሚባለው ስብስብ ባጠቃላይ የተሻለ መረጃ አለው። ለዚህም ነው የመከላከያ ሚኒስትርና የኮማንድ ፖስት ሃላፊ የሚባል ኮልኮሌ ከተደረተላቸው ግለሰብ የሁለት ሰዓት ዝባዝንኬ የአንድ ሕወሓት ካድሬ ጥቂት አንቀፆች የሃገሪቱን አካሄድ የተሻለ የሚያሳዩት።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: